Fana: At a Speed of Life!

‘የሀገር ግንባታ መሰረታዊያን’ በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘የሀገር ግንባታ መሰረታዊያን’ በሚል መሪ ሀሳብ ዘላቂ ሰላም ማምጣትን ታሳቢ ያደረገ ውይይት በመካሄድ ላይ ነው፡፡

በሰላም ሚኒስቴር በተዘጋጀው በዚህ ውይይት የዩኒቨርሲቲ መምህራን እና የሚዲየ አካላት ተሳትፈውበታል፡፡

በመድረኩ የሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ምን ተሰርቷል? ሀገራዊ እሴቶቻችንና ጥቅሞቻችን ምንድናቸው? የሚሉ ሀሳቦች ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቧል።

የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዷለም÷ ሁላችንንም የሚያስተሳስር የጋራ ቤት ሀገራዊ ማንነት እንዴት እንገነባለን የሚለው ላይ አተኩረን መወያየት አለብን ብለዋል፡፡

በተጨማሪም÷ ባለፉት አመታት ሀገር የገነባንባቸው ትርክቶቻችን ምን ጠንካራ ጎን ነበራቸው፣ ምን ክፍተቶች ነበሩ የሚለው ላይ መነጋገር እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

በውይይት መድረኩ የዜጎችን ወጥቶ መግባት ያረጋገጠ የሰላም አየር እውን እንዲሆን የጋራ የሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ የሚያስገነዝብ ሀሳብ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።

በፈቲያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.