Fana: At a Speed of Life!

132 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ ሀገራቸው ተላኩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 132 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች በሁለት ዙር ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ መላካቸውን አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ገለጹ፡፡

በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ እንዳስታወቁት፥ ስደት በዜጎች ላይ የሚፈጥረውን የአካል፣ የሥነ-ልቦና እና የሞራል ጉዳት ለመከላከል ታሳቢ በማድረግ ፍልሰተኞች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ነው፡፡

ወደ ሀገራቸው የተመለሱት ዜጎችም ራሳቸውን እና ማህበረሰባቸውን በመጠበቅ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚገባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ከቀናት በፊት 139 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.