Fana: At a Speed of Life!

ኒውደልሂ የዓየር ብክለትን ለመግታት የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ልትገድብ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕንዷ ኒውደልሂ የዓየር ብክለትን ለመግታት ከፈረንጆቹ ኅዳር 13 እስከ 20 ባሉት ቀናት ለአንድ ሣምንት የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ልትገድብ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በሕንድ የደልሂ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ጎፓል ራይ ÷ ምንም እንኳን ያልተበከለ ዓየር ለማግኘት እና ንጹሕ ከባቢ ለመፍጠር ጥረት ቢደረግም ጥረቱ ከባድ ሆኖብናል ፤ ችግሩም እንደቀጠለ ነው ብለዋል፡፡

በከተማዋ የሚተገበረው ደንብ፥ ጎዶሎ የታርጋ ቁጥር ያላቸውን ተሽከርካሪዎች ነጠላ ቁጥር ባላቸው ቀናት፣ እንዲሁም ሙሉ የታርጋ ቁጥር ያላቸውን ተሽከርካሪዎች ሙሉ ቁጥር ባላቸው ቀናት እንዲሽከረከሩ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡

የሕንዷ ኒው ደልሂ ብዙ ጊዜ በየዓመቱ ኅዳር ወር ላይ ክረምቱ ከመጀመሩ አስቀድሞ በዓለማችን ከፍተኛ የተባለለትን የዓየር ብክለት በማስመዝገብ ረገድ ከቀዳሚዎቹ ከተሞች ተርታ በመሠለፍ ትታወቃለች፡፡

ኒውደልሂ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ ላለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ከፍተኛውን የተበከለ ዓየር በአከባቢዋ በማስተናገድ ከባድ ሁኔታ ውስጥ እንደምትገኝ የሀገሪቷ የከባቢ ዓየር ቁጥጥር አካል አስታውቋል፡፡

የከተማዋ አሥተዳደርም የዘጋቸውን የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ ፈረንጆቹ ኅዳር 10 ቀን ድረስ እንዲያራዝም እንዳስገደደው የማሌዢያ የዜና ምንጭ አስነብቧል፡፡

አሁን ላይ በሕንድ የፊታችን ኅዳር 12 ቀን የሚከበር ብሔራዊ ፌስቲቫል መኖሩን ተከትሎ የዓየር ብክለቱ ቢባባስ እንጂ የመሻሻል ሁኔታ ላይታይ ይችላል የሚል ሥጋትን አጭሯል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.