የሜጢ ንፁህ መጠጥ ውሃ ማስፋፊያ ፕሮጀክትን እስከ ሕዳር ወር መጨረሻ ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ98 ሚሊየን ብር ወጪ እየተገነባ የሚገኘውን የሜጢ ከተማ ንፁህ መጠጥ ውሃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት እስከ ሕዳር ወር መጨረሻ ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን የጋምቤላ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ፡፡
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ የክልሉ አመራሮች በግንባታ ላይ የሚገኘውን የሜጢ ከተማ ንፁህ መጠጥ ውሃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት እና የትንሹ ሜጢ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምሕርት ቤትን ጎብኝተዋል።
አቶ ኡሞድ በጉብኝቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ በሜጢ ከተማ ከፍተኛ የሆነ የውሃ ችግር እንደሚስተዋል አንስተዋል፡፡
በመሆኑም የሜጢ ከተማ ንፁህ መጠጥ ውሃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት በአጭር ጊዜ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ የክልሉ መንግሥት ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡
ክልሉ ከፍተኛ የሆነ የከርሰ ምድርና የገፀ ምድር ውሃ ሀብት ቢኖረውም ሕዝቡ የሀብቱን ያህል ተጠቃሚ አለመሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡
እንዲሁም ለትምሕርት ቤቶች ደረጃ መሻሻል ሁሉም አመራር የድርሻውን እንዲያበረክት የጠየቁት አቶ ኡሞድ÷ ለትንሹ ሜጢ 2ኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት ከአንድ ወር ደመወዛቸው ግማሹን ለመለገስ ቃል ገብተዋል።
የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ቡን ዊው በበኩላቸው÷ የሜጢ ከተማን ነዋሪ ዘላቂና አስተማማኝ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!