ጠ/ሚ ዐቢይ ለኢትዮጵያ የመመርመሪያ ኪቶችን ለላከው ለቴንሴንት ፋውንዴሽ ምስጋና አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለኢትዮጵያ የመመርመሪያ ኪቶችን ለላከው የቴንሴንት ፋውንዴሽኑ ማ ሁዋንቴንግን ምስጋና አቀረቡ።
ቴንሴንት ፋውንዴሽ ለኢትዮጵያ የላካቸው የኮሮናቫይረስ የመመርመሪያ ኪቶች አዲስ አበባ ደርሰዋል።
ይህንን ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ፥ “ኢትዮጵያ ኮቪድ19ን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ፣ የመመርመሪያ ኪቶችን የላኩልንን የቴንሴንት ፋውንዴሽኑን ማ ሁዋንቴንግን አመሰግናለሁ” ብለዋል።
እንዲህ ያሉት የአጋርነት ሥራዎች፣ ኢትዮጵያ ቫይረሱን የመመርመር አቅሟን እንድታጠናክር የሚያግዙ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።