Fana: At a Speed of Life!

የስዊድን ኪነ-ህንጻ ባለሙያዎች ሰማይ ጠቀስ ፎቆችን ከእንጨት እየገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የስዊድን የኪነ-ህንጻ ባለሙያዎች እሽግ እንጨቶችን በማጣበቅ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች እየገነቡ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

በስዊድን የህንጻ መሃንዲሶች በሲሚንቶ፣ ጡብ እና ብረት በመጠቀም ህንጻ ከመገንባት የእንጨት ህንጻዎች ወደመገንባት እየተመለሱ እንደሆነም ነው የተገለጸው።

ወደ እንጨት ህንጻዎች ሽግግር ማድረግን ወደ ግንባታ ልምምዶች ለመመለስ እንደሆነ የገለጹት ባለሙዎቹ ፥ ግንበኞች በስዊድን በስኬልፍታ ውስጥ የሚገኘውን ሳራ የባህል ማዕከል በ110 ሚሊየን ዶላር የማረጋገጫ ጽንሰ-ሀሳብ ሠርተዋል።

የዋይት አርኪቴክተር መሪ አርክቴክት ሮበርት ሽሚትዝ ከሳራ የባህል ማዕከል በስተጀርባ ያለው ድርጅት ማዘጋጃ ቤቱ ‘አስደናቂ ሕንፃ’ እንዲሰራ ጠይቋል ያሉ ሲሆን፥ ለዚህም ወገባችን ጠበቅ አድርገን እየሰራን ነው ሲሉም ነው የተናገሩት።

የሳራ ማእከል እያንዳንዱ ክፍል የተገነባው በእንጨት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፤ የእንጨት ህንጻዎች ግንባታ በሳራ ማዕከል ብቻ እንደማይወሰን ተመላክቷል።

እነዚህ ሕንፃዎች በሲሚንቶ ላይ የተመሰረቱ እንዳልሆኑም ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ በመረጃው አንስቷል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ለሕንፃ ግንባታ የሚውሉ ቁሳቁሶች በከፍተኛ ሁኔታ የካርበን ዳይኦክሳይድ ልቀትን እያባባሱ እንደሆነም ነው የሚገለጸው፡፡

እንደአብነት የሲሚንቶ ማምረቻ 8 በመቶ የዓለም ሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀትን ይሸፍናል ሲል የሮቼስተር ዩኒቨርሲቲ ጥናት ያመላክታል።

የቁሳቁስ ማምረቻ በዓለም አቀፉ ብረት ማህበር ከ7 እስከ 9 በመቶ የሚሆነውን የዓለምአቀፍ ካርቦን ልቀትን ይይዛል።

ከእንጨት ለሚሰሩ ህንጻዎች ስጋት የሚሆነው እሳት ሲሆን፥ በህንፃዎች ላይ እሳትን የሚከላከሉ ሽፋኖችን በመጠቀም የእነዚህን ሕንፃዎች ደህንነት ለማረጋገጥ እንደሚቻልም ነው የተነሳው፡፡

እነዚህ የእንጨት ህንጻዎች በተለያዩ ሀገራት እንደሚተገበሩና በዚህም የዓየር ንብረት ተጽዕኖን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አንድ እርምጃ እንደሚሆንም ታምኖበታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.