Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ሰው የጫነ መንኩራኩር ልታመጥቅ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ሰው የጫነ መንኩራኩር ወደ ጠፈር ልታመጥቅ መሆኑን የሀገሪቷ የጠፈር ምርምር ተቋም አስታወቀ፡፡

ሼንዡ – 17 በተባለችው መንኮራኩር በነገው ዕለት ወደ ጠፈር የሚላኩት ሦስት ተመራማሪዎች ÷ ታንግ ሆንግቦ፣ ታንግ ሼንግጂ እና ጂያንግ ዢንሊን እንደሚባሉም ቲ አር ቲ ወርልድ ዘግቧል፡፡

በወጣት የጠፈር ተመራማሪዎች የምትመራው መንኮራኩር፥ በቻይና ሰሜን ምዕራብ ከሚገኘው ጁኳን የጠፈር ማዕከል እንደምትወነጨፍ ተገልጿል፡፡

መንኮራኩሯ ተልዕኮዋን ለመፈጸም እስከ ፈረንጆቹ ሚያዝያ 2024 በጠፈር ትቆያለችም ተብሏል፡፡

የአሁኑ ተልዕኮ የቻይና የጠፈር ምርምር ጣቢያ ከተቋቋመ ጀምሮ በዕድሜ እጅግ ወጣቶችን ያካተተ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.