Fana: At a Speed of Life!

የሰራዊት ቀንን ምክንያት በማድረግ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)”በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሰራዊት” በሚል መሪ ቃል 116ኛው የሰራዊት ቀን በልዩ ድምቀት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ይከበራል፡፡

ቀኑ ሰራዊቱ ለሀገር እየከፈለ ያለውን መስዋዕትነት ህብረተሰቡ ተገንዘቦ ተገቢውን እውቅና እና ክብር የሚሰጥበት እንዲሁም የሰራዊቱ አባላት ቃላቸውን ዳግም የሚያድሱበት ዕለት በመሆኑ ፕሮግራሙ በተቀመጠለት አቅጣጫ እንዲከበር የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን ገልጿል፡፡

በዚህም በመስቀል አደባባይ የሚካሄደው መርሃግብር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ግብረ ኃይሉ አስታውቋል።

በመሆኑም ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ኡራኤል አደባባይ ላይ ፣ ከቦሌ ጌቱ ኮሜርሻል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ በታች እና በላይ እንዲሁም ግራና ቀኝ ፣ ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ የቀድሞው አራተኛ ክፍለጦር (ጥላሁን አደባባይ ላይ ዝግ ) ፣ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ለገሀር መብራት ላይ፣ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ ላይ፣ ከራስ ሆቴል ወደ ስታድዮም ራስ ሆቴል ላይ ፣ ከሃያሁለት አደባባይ ወደ ኡራኤል የታችኛው መንገድ ሙሉ ለሙሉ

መስቀል አደባባይ፣ ሜክሲኮ አደባባይ፣ አፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት ፣ልደታ ፀበል እና የመከላከያ ግቢ ድረስ በመምጫና በመመለሻ ወቅት ፣ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ ፣ ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ፣ ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባንቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ

እንዲሁም ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወስደው መንገድ ECA ጫፍ ላይ ለጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም አጥቢያ ረቡዕ ከለሊቱ 8 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

ፕሮግራሙ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ገልጾ ለመላው የመከላከያ ሰራዊት አመራሮችና አባላት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.