የሴቶችን የፖለቲካ አቅም ለማጎልበትና ወደ አመራርነት ለማምጣት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችን የፖለቲካ አቅም ለማጎልበትና ወደ አመራርነት ለማምጣት እየተሠራ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዛህራ ሑመድ ገለጹ፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ፕሬዝዳንቷ የሴቶችን አቅም ለማጎልበትና ወደ አመራርነት ለማምጣት የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ አመልክተዋል።
የሊጉ ጽኅፈት ቤት ኃላፊና ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መስከረም አበበ በበኩላቸው ÷ የሴቶች ሊግ በሀገር አቀፍ የልማት ሥራዎች ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡
ለአብነትም የኅዳሴ ግድብ የቦንድ ግዢ ንቅናቄ፣ የሌማት ትሩፋት፣ የአረንጓዴ አሻራና ሌሎች መደበኛና የክረምት የልማት ሥራዎችን ማከናወኑን አንስተዋል፡፡
በፓርቲው የተቀመጡ የልማት ግቦችን እንደሚያሳኩ የክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡
በመድረኩ ባለፉት ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከናወኑ የክረምት ልማትና የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ላይ ሰፊ ሥራዎች መሠራታቸውን ኃላፊዎቹ አብራርተዋል።
በክልል ደረጃ ያሉ የሴቶች ቢሮዎች ከሊጉ ጋር በጋራ መሥራት የሚችሉባቸውን ሰንሰለት ማሥፋትና መደጋገፍ ያስፈልጋል ሲሉም ምክረ ሐሳብ አስቀምጠዋል።
የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ የ2016 ዓ.ም ሩብ ዓመትና የክረምት የልማት የሥራ ክንውን ሪፖርት ግምገማ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ መካሄዱን ከጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።