2ኛው ዙር የአመራሮች ስልጠና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ማዕከላት ሲሰጥ የነበረው ሁለተኛው ዙር የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
”ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሐሳብ በ10 ማዕከላት ከመስከረም 29 ቀን 2016 ጀምሮ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
ስልጠናው÷ በአመራሩ ዘንድ የተግባርና የሐሳብ አንድነት በማምጣት ሀገራዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያስችል አቅምና ክኅሎት መፍጠሩ ተገልጿል፡፡
የሥራ ተነሳሽንትንና ሀገራዊ ስሜትን የበለጠ ያጎላ እንዲሁም አመራሩ እርስ በርሱ ተሞክሮ እንዲለዋወጥ ብሎም ዕድል የፈጠረ ስልጠና መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ መረጃ ያመላክታል፡፡
አመራሩ በስልጠናው በፓርቲ መሰረታዊ እሳቤዎች በመመራት ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ነባራዊ ዐውዶችን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የአመራር ሚናውን ለመወጣት እራሱን ያዘጋጀበት የስልጠና ጊዜ መሆኑም ተመላክቷል፡፡