Fana: At a Speed of Life!

እስራዔልና ፍልስጤምን ለማሸማገል የተጠራው ጉባዔ ያለስምምነት ተበተነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ተባብሶ የቀጠለውን የእስራዔል እና ፍልስጤም ጦርነት እልባት እንዲያገኝ ዓልሞ ትናንት በግብጽ የተካሄደው የሠላም ጉባዔ ያለስምምነት ተበትኗል፡፡

በጉባዔው ላይ አሜሪካ እና እስራዔል ሳይሳተፉ መቅረታቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

የግብጽ ፕሬዚዳንት ቃል አቀባይ አሕመድ ፋህሚ በሠጡት መግለጫ÷ እየተባባሰ በመጣው የሰብዓዊ ቀውስ ላይ ለጉባዔው ተሳታፊዎች ጭብጥ በማስያዝ ረገድ ግብጽ ተሳክቶላታል ብለዋል፡፡

በጉባዔው ላይ÷ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ጆርዳን፣ ኳታር፣ ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሩሲያ እና ብሪታኒያን ጨምሮ ከ30 በላይ ሀገራት ተወካዮች መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡

ሁለተኛ ሣምንቱን ባስቆጠረው የእስራዔልና ፍልስጤም ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በሁለቱም ወገን በርካቶች መጎዳታቸው ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.