Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤሮ-ስፔስ ቴክኖሎጂዎች ማምረቻ ለማበልጸግ እየሠራሁ ነው አለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤሮ-ስፔስ ቴክኖሎጂዎች ማምረቻ ኢንዱስትሪ በሀገር ውስጥ ለማበልጸግ እየሠራ መሆኑን ገለጸ፡፡

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ መስፍን ጣሰው ÷ የተለያዩ የአውሮፕላን አካል መለዋወጫዎችን በሀገር ውስጥ በሥፋት ለማምረት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የአውሮፕላን የውስጥ አካልን በሀገር ውስጥ በሥፋት ለማምረት እንቅስቃሴ መጀመሩን ያነሱት ዋና ሥራ አሥፈጻሚው፤ ይኅም ለኢትዮጵያ ኤሮ-ስፔስ የማምረቻ ኢንዱስትሪ ዘርፍ መጎልበት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አመላክተዋል፡፡

የአውሮፕላን የውስጥ አካል መለዋወጫዎች በሀገር ውስጥ መመረት የውጭ ምንዛሬ ለማስቀረት ፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማምጣት እንደሚያስችልም ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የአውሮፕላን የውስጥ አካላትን ማምረት የሚያስችለውን ስምምነት በነኀሴ 2015 ዓ.ም ላይ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር መፈራረሙ ይታወሳል።

የኤሮስፔስ ምኅንድስና ዘርፍ የአውሮፕላን፣ የጠፈር መንኮራኩር እንዲሁም ከነዚህ ጋር ተጓዳኝ የሆኑ ሥርዓቶችና መሳሪያዎች ንድፍ፣ ፈጠራ፣ ማምረትና ፍተሻ ላይ የሚያተኩር የምኅንድስና ዘርፍ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.