የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እስራዔል ገብተዋል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራዔል-ሃማስ ጦርነት በቀጠለበት ሁኔታ የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እስራዔል ቴል አቪቭ መግባታቸው ተሰማ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቴል አቪቭ የገቡት የእስራዔል ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለማግኘት መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ሪሺ ሱናክ አቻቸውን ቤኒያሚን ኔታኒያሁ እና ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግን እንደሚያገኙ ከእስራዔል ጠቅላይ ሚኒስትር ፅኅፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ በሚኖራቸው ቆይታ በእስራዔል-ሃማስ ጦርነት በደረሰው የሰው ሕይወት መጥፋት እንዲሁም አሁን ላይ እየተስተዋለ ባለው የሰብዓዊ ቀውስ ጉዳይ ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ወደ ጋዛ ሰብዓዊ አቅርቦት እንዲደርስ ከጦርነት ነፃ መሥመር እንዲከፈት እንደሚመክሩም ተገልጿል፡፡
በጦርነቱ ሰበብ መውጫ አጥተው በጋዛ የታገቱ የብሪታኒያ ዜጎች ወደ ሀገራቸው መግባት በሚችሉበት ሁኔታ ላይም ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡