ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የመከላከያ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያን የዝግጁነት አቅምና የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የመከላከያ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያን የዝግጁነት አቅምና የሥራ እንቅስቃሴን ጎበኙ።
በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በተመራው ጉብኝት የመከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና የሰራዊቱ ከፍተኛ መኮንኖች ተሳትፈዋል።
የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል አበባው ታደሠ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ፣ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፣ የመከላከያ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል እና ሌሎችም ተገኝተው በቢሾፍቱ የሚገኘውን የመከላከያ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ የዝግጁነት አቅምና የሥራ እንቅስቃሴ መጎብኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በጉብኝታቸው ÷ የመከላከያ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ያከናወናቸውን ውጤታማ የፈጠራ ሥራዎች ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በመርሐ-ግብሩ በመከላከያ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ መሃንዲሶችና ሙያተኞች ዕውቅና እና ሽልማት እንደተሰጣቸው ተመላክቷል፡፡
የመካላከያ ሰራዊት ቀን ጥቅምት 15/2016 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ይሆናል።