አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ እና ሌሎች የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በኮምቦልቻ እና ደሴ ከተማ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ፡፡
በጉብኝቱ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ ልማትና ቤቶች ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አህመድ መሀመድ (ዶ/ር)፣ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
አቶ አደም ፋራህ በጉብኝታቸው ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት÷ በባሕር ዳር፣ ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች ያየኋቸው የልማት ሥራዎች ለሌሎችም ተሞክሮ እና አስተማሪ መሆን የሚችሉ ናቸው ብለዋል፡፡
መንግሥት የተሰጠውን የሕዝብ ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዲችል ለመንግስት ያላሰለሰ ድጋፍ እያደረጉ ያሉ ሀገር ወዳድ ባለሃብቶች በየከተሞቹ መኖራቸውን ተመልክቻለሁ ማለታቸውን የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ መረጃ ያመላክታል፡፡
ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች በአጭር ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ የለውጥ ሂደት ላይ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡
እያንዳንዱ የአካባቢው አመራር ከሕዝብ ጋር ተቀናጅቶ ከሠራ ከዚህ የላቀ ሁለንተናዊ ብልጽግናን በአጭር ጊዜ ማረጋገጥ እንደሚቻል ትልቅ ማሳያ ሲሉም ነው የገለጹት፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!