Fana: At a Speed of Life!

እስራዔል እና ሃማስ የሚያደርጉትን እንዲያስተውሉ ተመድ አስጠነቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራዔል እና ሃማስ የሚያደርጉትን እንዲያስተውሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስጠነቀቀ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሃማስ ያገታቸውን እስራዔላውያን በሙሉ እንዲለቅም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተመሳሳይ እስራዔል ወደ ጋዛ ሰብዓዊ እርዳታ ይደርስ ዘንድ እንድትፈቅድም ነው የጠየቁት።

አያይዘውም አሁን ላይ እስራዔል በጋዛ እየወሰደች ባለው ወታደራዊ እርምጃ በመካከለኛው ምሥራቅ ሁኔታዎችን እያከፋችው ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በጋዛ የመጠጥ ውሃ ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንዲሁም ሌሎች ለሰው ልጆች አሥፈላጊ የሆኑ አቅርቦቶች መቋረጣቸውን አስታውቀዋል።

ተመድ በግብፅ ፣ በጆርዳን ፣ በዌስት ባንክ እና በእስራዔል ካሉት መጋዘኖቹ የምግብ ፣ ንጹሕ የመጠጥ ውሃ እና የሕክምና አቅርቦት በሠዓታት ዕድሜ ወደ ጋዛ ማድረስ እንደሚችል መናገራቸውን ዘ ዲፌንስ ፖስት ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
በመወዳጀት ይከታተሉን፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.