Fana: At a Speed of Life!

በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የተገነቡ የአቅመ ደካሞች ቤትና ትምህርት ቤቶች ርክክብ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት እና ተጠሪ ተቋማቱ በክረምት በጎ ፈቃድ ፕሮግራም የተገነቡ የአቅመ ደካሞች ቤትና ትምህርት ቤቶች ርክክብ ተደርጓል።

ቤቶችና ትምህርት ቤቶቹ የተገነቡት በሸገር ከተማ አስተዳደር በፉሪ ክፍለ ከተማ በገዳ ፋጂ ወረዳ ውስጥ ሲሆን ለግንባታና ለተለያዩ ቁሳቁስ 21 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጓል፡፡

ለአስር አባ ወራዎች በተደረገው የቤት ርክክብ ሥነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ሀላፊ አለምፀሀይ ጳውሎስ እንደገለጹት፥ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞችን ቤት በመገንባት ለበርካቶች እፎይታን መፍጠር ተችሏል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) ሀሳብ አመንጪነት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለአቅመ ደካሞች የቤት ግንባታ ከተጀመረ መቆየቱንም ገልጸዋል፡፡

መኖሪያ ቤቱ የተገነባላቸው ነዋሪዎችም በተደረገላቸው የቤት ግንባታ መደሰታቸውን ነው የተናገሩት።

በአዳነች አበበ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.