Fana: At a Speed of Life!

የህግ የበላይነትን ማስከበርና ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ የበጀት ዓመቱ የመንግስት ዋና ተግባር መሆኑን ፕሬዚዳንት ሳኅህለወርቅ ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣ የሰላም መንገዶችን አሟጦ መጠቀም እንዲሁም ሀገራዊ ሰላምን ማረጋገጥ የበጀት ዓመቱ የመንግስት ዋና ተግባራት ናቸው ሲሉ ፕሬዚዳንት ሳኅህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡

የ6ኛው ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው፡፡

በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ሳኅህለወርቅ ዘውዴ÷ የ2016 በጀት ዓመት የመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎችን አስመልክተው ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡

በማብራሪያቸውም÷” በቀጣይ ሶስት ዓመታት የሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት ማስቀጠል ዋነኛ አላማችን ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ልማትና ጥፋትን መሳ ለመሳ ይዞ መጓዝ ለዘላቂ ሀገራዊ እድገት እንቅፋት ነው ያሉት ፕሬዚዳንቷ÷እንቅፋቶችን ማንሳት እና የሀገራችንን ዘላቂ እድገት ማፋጠን ለአፍታም የምናቆመው ጉዳይ አይደለም ብለዋል፡፡

የሃይል አማራጭን በመጠቀም ፖለቲካዊ ፍላጎትን ለማሟላት የሚደረጉ ህገ ወጥ ተግባራትን መንግስት እንደማይታገስም አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.