Fana: At a Speed of Life!

በ2015 የበጀት ዓመት በተለያዩ ዘርፎች ስኬት ተመዝግቧል – ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ከሦስት ዓመታት በፊት የ10 ዓመታት የልማት ዕቅድ አዘጋጅቶ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፡፡

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ሥነ – ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡

በመክፈቻ ሥነ- ሥርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ባደረጉት ንግግር÷ መንግሥት የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ከሦስት ዓመታት በፊት የ10 ዓመታት የልማት ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር ገብቷል ብለዋል፡፡

በዕቅዱ የመጀመሪያ ሦስት ዓመታት (ከ2013 እስከ 2015 ዓ.ም) በሁሉም ዕድገት አመላካች ዘርፎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መገኘታቸውን አንስተዋል፡፡

ያለፈውን አንድ ዓመት አፈጻጸም ብቻ ብንመለከት በጥቅሉ ጥሩ ውጤቶች ተመዝግበዋል ነው ያሉት፡፡

በፈታኝ እና በተለያዩ ተግዳሮቶች ውስጥ እያለፍን ቢሆንም የተገኘው ስኬት ጠንክረን መውጣታችንን ያሣያል ነው ያሉት ፕሬዚዳንቷ በንግግራቸው፡፡

ተግተን ከሠራን ደግሞ ከዚህ የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደምንችል ተምረንበታል ሲሉም አመላክተዋል፡፡

በአንድ በኩል እንደ ሀገር የገጠሙንን ፈተናዎች መቋቋም በሌላ በኩል ደግሞ በእነዚህ ፈተናዎች ውስጥ ሁኔታዎችን ወደ ዕድል መቀየር እንዲሁም ዕድገትና ለውጥ ለማስመዝገብ መቻል ታላቅ ስኬት ነው ብለዋል፡፡

በዮሃንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.