Fana: At a Speed of Life!

የፌጦ የጤና በረከቶች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፌጦ ዝቅተኛ የካሎሪ ይዘት ያለው ሲሆን እንደ ቫይታሚን ኤ፣ ሲ እና ኬ እንዲሁም ኦሜጋ -3 ፋቲ አሲድ ያሉ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ይዟል።

የፌጦን ፍሬን ሆነ ቅጠል መጠቀም በርካታ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት ጥናቶች ያስረዳሉ ፡፡

ፌጦ በንጥረነገሮች የበለጸገ በመሆኑ በሽታን የመከላከል አቅምን የማሳደግ ፣ ክብደትን የመቀነስ ፣ የሰውነት አካል ክፍሎች ተግባራቸውን በአግባቡ እንዲያከናውኑ የማገዝ ፣ እብጠትን የመከላከል እና የልብ ጤናን የመጠበቅና መሰል ጥቅሞችን ይሰጣል፡፡

በተጨሪም÷የሆድ ድርቀትን ለመከላከልና የምግብ አለመፈጨት ችግርን ለመቅረፍ እንዲሁም ለምታጠባ እናት የጡቷ ወተት መጠን እንዲጨምር የማድረግ ጥቅሞች እንዳሉት የኸልዝ ላይን መረጃ አመላክቷል፡፡

እንዲሁም የስኳር በሽታን፣ የአጥንት ስብራትን፣ አስምን፣ የሆድ ድርቀትን እና አንዳንድ የካንሰር ዓይነቶችን ለማከም የሚያገለግሉ ጤናማ መከላከያ ባዮአክቲቭ ውህዶች አሉት፡፡

ፌጦን አዘውትሮ መመገብ የአንጀት እንቅስቃሴን መደበኛ ለማድረግ የሚረዳ ሲሆን÷በተጨማሪም ህጻናት ሆዳቸውን ሲታመሙ ፌጦን ከውሃ ጋር በመቀላቀል ቢሰጣቸው ከሆድ ህመማቸው እንደሚያገግሙ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

ፌጦ አስፈላጊ የሆኑ የቅባት አሲዶች እና አሚኖ አሲዶች እንዲሁም እንደ ብረት፣ ፖታሺየም፣ካልሲየም እና ፎስፎረስ ያሉ ማዕድናትን በውስጡ ይዟል።

በምግብ ማምረቻ ኢንዱስትሪዎች እና በባህላዊ የምግብ ዝግጅቶች ውስጥ ፌጦ አልፎ አልፎ ጥቅም ላይ ቢውልም ለጤና ከሚሰጠው ፋይዳ አንጻር ግን በሰፊው ጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት የዘርፉ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.