የሆረ አርሰዴ ኢሬቻ በዓል ተሳታፊዎች ወደ ቢሾፍቱ እየገቡ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ነገ በቢሾፍቱ ለሚከበረው የሆረ አርሰዴ ኢሬቻ በዓል ተሳታፊዎች ወደ ከተማዋ በመግባት ላይ ይገኛሉ።
ባንኮች እና ሆቴሎችን ጨምሮ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ልዩ ዝግጅት በማድረግ ለእንግዶቹ አገልግሎት በመሥጠት ላይ ናቸው።
የበዓሉ ተሳታፊዎች የኢሬቻን በዓል ዕሴት በሚያንጸባርቁ በተለያዩ አልባሳት አሸብርቀው ከተማዋን አድምቀዋታል።
በከተማዋ እየተዘዋወሩም የተለያዩ ባሕላዊ ዜማዎችን በማዜም የበዓሉን ዋዜማ በማክበር ላይ ይገኛሉ።
ተሳታፊዎች በነገው ዕለት በዓሉን ባህላዊ ዕሴቱን በጠበቀ መልኩ በሠላም ለማክበር መዘጋጀታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
የሆረ አርሰዴ ኢሬቻ በዓል “ኢሬቻ የአንድነት እና የወንድማማችነት ዓርማ” በሚል መሪ ሐሳብ በነገው ዕለት በቢሾፍቱ ይከበራል።
በመላኩ ገድፍ