Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልላዊ መንግስት ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 25 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልላዊ መንግስት የሰላም፣ የፍቅር፣ የእርቅ፣ የወንድማማችነት፣ የእህትማማችነት እና የአንድነት ማሳያ ለሆነው የኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

 

ኢሬቻ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሀብት ከመሆኑም ባሻገር አንድነትን ፣ አብሮነትን እና መተባበርን የሚያጎለብት ታላቅ በዓል ነው ሲል የክልሉ መንግስት ገልጿል።

 

የክልሉ መንግስት ዘንድሮ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችን ባሳተፈ መልኩ በሰላም እና ባማረ በመሆኑ እለቱን ልዩ እንደሚያደርገውም አመላክቷል።

 

የበዓሉ ተሳታፊዎችም አንድነትንና፣ ወንድማማችነትን በማጎልበት በሰላም እንዲከበር የበኩላቸውን እንዲወጡም  ጥሪ ያቀረበው የሃረሪ ክልላዊ መንግስት  የኢሬቻ በዓል እንደወትሮው ሁሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የወንድማማችነት፣ የእህትማማችነት እና የአብሮነት በዓል እንዲሆን መልካም ምኞቱን መግለጹን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.