የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ለንደን የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ 10 አሳደገ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ለንደን ከተማ ከሚያደርገው 7 ሳምንታዊ በረራ በተጨማሪ 3 ሳምንታዊ በረራዎችን ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ ለንደን ከተማ ወደሚገኘው ጋትዊክ አውፕላን ማረፊያ የሚያደርገውን አዲስ ሳምንታዊ በረራ ከሕዳር 11 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚያካሂድ ገልጿል፡፡