Fana: At a Speed of Life!

ፖሊስ ከወገንተኝነት ነጻ በመሆን የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በትኩረት ሊሰራ ይገባል – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖሊስ ከየትኛውም ወገንተኝነት ነጻ በመሆን የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ÷በቅርቡ ስልጠና ወስደው ለተመረቁ የሐረሪ ክልል ምልምል ፖሊስ አባላት የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።

በዚህ ወቅትም ፖሊሶች በንድፈ ሃሳብና በተግባር የቀሰሙትን እውቀትና ክህሎት በመጠቀም የሠላምና ደህነት አርበኝነታቸውን በተግባር ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ፖሊስ ዘመን ተሻጋሪ ስራ ማከናነውን እንዲችልም ከየትኛውም ወገንተኝነት ነጻ መሆን እንዳለበት ነው አጽንኦት የሰጡት፡፡

ዜጎች በሠላም ወጥተው እንዲገቡ ሕግን በፍትሃዊነት ማረጋገጥ እና ሠላም ማስፈን ከአባላቱ የሚጠበቅ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የሐረሪ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ነስሪ ዘካሪያ በበኩላቸው÷ ምልምል ፖሊሶች በስልጠና ወቅት ማንኛውንም ፖሊሳዊ ስራ መስራት የሚያስችላቸውን እውቀትና ክህሎት እንዲያገኙ መደረጉን አንስተዋል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.