እርስ በርሳችን በመደጋገፍ ከችግሮቻችን ልንሻገር ይገባል – አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር
አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እርስ በርሳችን በመረዳዳትና በመደጋገፍ ከሁለንተናዊ ችግሮቻችን ልንሻገር ይገባል ሲሉ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡
አፈ ጉባዔ አገኘሁ ለሕዝበ ሙስሊሙ ለ1 ሺህ 498ኛው የነብዩ መሐመድ (ሰዐወ) መውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም÷ የእምነቱ ተከታዮች የመውሊድን በዓል ሲያከብሩ በመተሳሰብና መደጋገፍ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ችግሮቻችንን ለመሻገር እና መጪውን ብሩኅ ለማድረግም ሁሉም በተሰማራበት መስክ የተጣለበትን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ትውልዱን ወደቀጣዩ የከፍታ ምዕራፍ ለማሻገር ለእውነት፣ ለፍትሕና ለሕግ የበላይነት ተገዢ መሆን እንደሚጠበቅ ገልጸው÷ በዓሉ የአንድነት፣ የፍቅርና የመተሳሰብ እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡