Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካ ዘመናዊ ታንኮች ከቀናት በኋላ ዩክሬን ይደርሳሉ ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በእርዳታ የላከቻቸው አብራምስ ኤም 1 ታንኮች በቀናት ውስጥ ዩክሬን እንደሚደርሱ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ይህንን ያሉት ትናንት ከዩክሬን አቻቸው ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ጋር በዋይት ሀውስ ተገናኝተው በተወያዩበት ወቅት ነው ፡፡

በተጨማሪም ፕሬዚዳንት ባይደን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ያካተተ 325 ሚሊየን ዶላር የእርዳታ ፓኬጅ ማጽደቃቸውን የአርቲ ዘገባ አመላክቷል፡፡

የጦር መሳሪያ እርዳታው ዩክሬን ለረዥም ጊዜ ስጠይቅ የቆየችውን የረጅም ርቀት ሚሳኤሎች እንደላካተተ መገለጹንም ዘገባው አስታውሷል፡፡

አሜሪካ ስለ ነጻነት ስትል አሁንም ወደፊትም ለዩክሬን ድጋፍ ማድረጓን ትቀጥላለች ሲሉም ፕሬዚዳንት ባይደን ለዩክሬን ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.