Fana: At a Speed of Life!

የሶርያው ፕሬዚዳንት ባሻር አል-አሳድ ለጉብኝት ቻይና ገቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ12 ዓመታት በዘለቀ ጦርነት ውስጥ የምትገኘው ሶሪያ ፕሬዚዳንት ባሻር አል-አሳድ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ቻይና ይገኛሉ።

የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ሀገሪቱ ወደ ጦርነት ከገባችበት ጊዜ ጀምሮ የመጀመሪያ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በሶሪያ ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ቤጂንግ ለሀገሪቱ አጋርነቷን ማሳየቷን ቀጥላለች ነው የተባለው፡፡

ፕሬዚዳንት አሳድ በምስራቃዊ ቻይና ሃንግዙ ከተማ በመጪው ቅዳሜ በሚጀመረው የእስያ ስፖርታዊ ውድድር የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ እንደሚገኙም የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ቀደም ሲል በሶሪያ በኩል በወጣው መረጃ መሰረትም ፕሬዚዳንቱና ሌሎች የሶሪያ ልዑካን በቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ለጉባኤ መጋበዛቸው ተመላክቷል፡፡

በጦርነት ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደችውን ሶሪያን መልሶ ለመገንባት ያስፈልጋል ለተባለው በ10 ቢሊየኖች የሚቆጠር ዶላር ድጋፍ ቻይና ከፍተኛውን ድርሻ ትይዛለች ተብሎ ይጠበቃል።

የሶሪያው ፕሬዚዳንት ባሻር አል-አሳድ የመጨረሻው የቻይና ጉብኝት በፈረንጆች በ2004 እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.