Fana: At a Speed of Life!

ለልጆችዎ ሊነግሯቸው የሚገቡ የእግረኛ መንገድ አጠቃቀሞች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፈው በጀት አመት በ10 ሺህ ተሽከርካሪዎች በአማካይ 28 በመቶ አደጋ እንደደረሰ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

በዚህም በአመዛኙ ከ5 እስከ 29 አመት እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ዜጎች በዚሁ አደጋ ህይወታቸውን ከሚያጡት ውስጥ ቀዳሚ መሆናቸውም ነው የተነገረው፡፡

ወቅቱ የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተጀመረበት እንደመሆኑ እና የተማሪዎች እንቅስቃሴ በስፋት የሚስተዋልበት በመሆኑ ስለ እግረኛ መንገድ አጠቃቀም ለልጆች መነገር ያለባቸው ተግባራት አሉ፡፡

እነሱም ልጆች የመንገድ ላይ እንቅስቃሴ ከመጀመራቸው በፊት የእግረኛ መንገድ አጠቃቀም ህግን ማስተማር፣ ዘወትር ወደ ተሽከርካሪ መንገድ ከመግባታቸው በፊት መቆም፣ ሁሉንም አቅጣጫ መመልከትና በጥንቃቄ ማዳመጥ እንደሚኖርባቸው ማስተማር ያስፈልጋል፡፡

እንዲሁም ልጆች መንገድ ከመሻገራቸው በፊት ከአሽከርካሪው ጋር የአይን ለአይን ግንኙነት መፍጠር መቻላቸውን ማረጋገጥ፣ ቤተሰብ ከልጆች ጋር አብሮ በሚጓዝበት ወቅት የትራፊክን ምንነትንና የመንገድ ላይ ምልክቶችን ትርጉም ማስተማር ይጠበቅበታል።

በተጨማሪም ልጆችን ዘወትር ለእግረኛ ማቋረጫ የተዘጋጁ ቦታዎች ባሉበት ቦታ ላይ ብቻ ማቋረጥ እንዳለባቸው መንገር፣ በቆሙ ተሸከርካሪዎች መካከል ለመሻገር በፍጹም እንዳይሞክሩ ማስጠንቀቅ የቤተሰብ ሃላፊነት እንደሆነ ከአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.