Fana: At a Speed of Life!

ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመከታተልና አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሁሉን ሥምሪት ይጠይቃል- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመከታተልና አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሁሉን ሥምሪት እንደሚጠይቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በትናንትናው እለት በህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መቆጣጠር ዙሪያ ከክልል አመራሮች ጋር መወያየታቸውን በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ አስታውቅዋል።

ውይይቱን አስመልክቶ ዛሬ ባወጡት መረጃም፥ ትናንት ከክልል አመራሮች ጋር በነበረን ውይይት፣ በሕገ ወጥ መንገድ የጦር መሣሪያ ማስገባት እና ማዘዋወርን ለመግታት ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ተነጋግረናል ብለዋል።

ባለፉት ጥቂት ወራት ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪዎችን ተከታትሎ በመያዝ አኩሪ ሥራ መሰራቱንም አስታውቅዋል።

ከእያንዳንዱ ምንጭ ወደ ሀገር የሚገባውን የመሣሪያ ዝውውር በአግባቡ ለመከታተል እና ሕገ ወጥ መሣሪያ አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሁሉንም ሥምሪት እንደሚጠይቅም አስገንዝበዋል።

https://www.facebook.com/PMAbiyAhmedAli/

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.