ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የመሠረተ ልማት ትስስሮች ልዩ ቴክኒካል ኮሚቴን በሊቀ-መንበርነት እንድትመራ ተመረጠች
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 5 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አህጉራዊና አካባቢያዊ የመሠረተ ልማት ትስስሮች ልዩ ቴክኒካል ኮሚቴን በሊቀ-መንበርነት እንድትመራ ተመርጣለች፡፡
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በታንዛንያ ባካሄው 4ኛው የልዩ ቴክኒካል ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ ኮሚቴውን ለሚቀጥሉት 2 ዓመታት በሊቀ-መንበርነት እንድትመራ በሙሉ ድምጽ ተመርጣለች፡፡
በ4ኛው የልዩ ቴክኒካል ኮሚቴ ስብሰባ ወቅት በህብረቱ ኮሚሽን አማካኝነት የሚከናወነው የአፍሪካ የመሠረተ ልማት ፕሮግራም ለቀጣዮቹ 10 ዓመታት እንዲራዘም መደረጉ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም÷ ሁሉንም ዓይነት የትራንስፖርት ዘዴዎችን የሚመለከቱ በርካታ መርሐ-ግብሮች መጽደቃቸውን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡