የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2023 የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ሽልማትን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2023 የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ሽልማትን ለአራተኛ ጊዜ አሸንፏል።
መቀመጫውን ብሪታኒያ ያደረገው እና አየር መንገዶችን በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች በየዓመቱ አወዳድሮ የሚሸልመው “ቢዝነስ ትራቭለር አዋርድ 2023” በለንደን ከተማ ተካሂዷል፡፡
በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2023 የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ሽልማትን ለአራተኛ ጊዜ ማሸነፉን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡
የኬንያ እና የደቡብ አፍሪካ አየር መንገዶች ደግሞ በቅደም ተከተል ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ መያዛቸው ተገልጿል፡፡