Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት 119 ደረጃዎችን አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት 119 ደረጃዎች ማፅደቁን አስታወቀ፡፡

ኢንስቲትዩቱ በ37ኛው የደረጃዎች ምክርቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ከቀረቡ 312 ነባርና አዳዲስ ደረጃዎች ውስጥ 119 ደረጃዎች መፅደቃቸውን አስታውቋል።

ደረጃዎቹ የፀደቁት በግብርና ዘርፍ ፣በኬሚካል እና በኤሌክትሮ መካኒካል ዘርፎች መሆኑም ታውቋል፡፡

ደረጃዎቹ በአካባቢ ጥበቃ፣ ከህብረተሰብ ጤና እና ደህንነት እንዲሁም ንግድን ከማቀላጠፍ አንፃር ያላቸው ሚና ተመርምሮ መፅደቃቸው ተመላክቷል፡፡

ደረጃ መዘጋጀቱ የአምራቾችንና አስመጪዎችን ክህሎት ለማዳበር ጉልህ ሚና  እንዳለውም ነው በዚህ ወቅት የተገለጸው፡፡

በዘቢብ ተክላይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.