11ኛው የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 11ኛው የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት ሥነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።
በሽልማት ስነ-ሥርዓቱ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀና እንድትል ላደረጉ እና የተለያዩ በጎ ስራዎችን ላከናወኑ በጎ ሰዎች እውቅና ተሰጥቷል።
ባለፋት 10 ዓመታት በተደረጉ የበጎ ሰው እውቅና መስጫ ስነ-ሥርዓቶች 225 በጎ ዜጎች በተለያዩ ዘርፎች መሸለማቸው ተገልጿል፡፡
በዛሬው የበጎ ሰው ሽልማት ስነ-ሥርዓትም በተለያዩ ዘርፎች ላሸነፉ በጎ ሰዎች እና ተቋማት እውቅና ተሰጥቷል፡፡
በዚህ መሰረትም ፡-
• በመምህርነት ዘርፍ መምህር አዝማች ይርጋ ገብሬ
• በባህልና ቅርስና ቱሪዝም የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም
• በንግድ ኢንዱስትሪና ስራ ፈጠራ ዘርፍ ኩሪፍቱ ሪዞርትና ስፓ
• በበጎ አድራጎት ዘርፍ ወይዘሮ እቴነሽ ወ/አገኘሁ ( የብርሀን ለህፃናት በጎ አድራጎት መስራችና ስራ አስኪያጅ)
• በኪነጥበብ ዘርፍ ሰአሊ ወርቁ ጎሹ
• መንግስታዊ የስራ ሀላፊነትን በአግባቡ በብቃት በመወጣት ዘርፍ ያየህይራድ ቅጣው (ዶ/ር)) (የትምህርት ሚንስትርና የብሄረሰብ ጥናት ኢንስቲትዩት ኃላፊ የነበሩ)
• በሚዲያና ጋዜጠኝነት ዘርፍ ጋዜጠኛ ኤፍሬም እንዳለ
• በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሙሉዓለም ገሰሰ (ዶ/ር)
• በትውልደ ኢትዮጵያውያን ዘርፍ አሰፋ ጀጃው (ዶ/ር) (የህክምና ባለሞያ በአሜሪካ የህክምና ድጋፍ ለሚፈልጉ ድጋፍ ያደረጉ) ተሸላሚ ሆነዋል።