Fana: At a Speed of Life!

በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ላይ ሲነሱ ለነበሩ ቅሬታዎች ዋናው ምክንያት የፓስፖርት ዕጥረት ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ላይ በተገልጋዮች ሲነሱ ለነበሩ ቅሬታዎች ዋናው ምክንያት የፓስፖርት ህትመት ዕጥረት መሆኑን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ገልጿል፡፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙ ባለፉት 30 ቀናት ውስጥ ሲሰራቸው የነበሩ ስራዎችን በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የፓስፖርት ህትመት ዕጥረት ዋና ችግር መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሯ፥ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ችግር፣ሌብነት እና ብልሹ አሰራር ለቅሬታዎቹ በምክንያትነት እንደሚጠቀሱ ተናግረዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍም 190 ሺህ ፓስፖርት በአንድ ወር ውስጥ ታትሞ ወደ ሀገር ቤት መግባቱንም ነው ዋና ዳይሬክተሯ ያስታወቁት፡፡

ፓስፖርት ለመውሰድ ከተመዘገቡ ከስድስት ወር በላይ ለሆናቸው ዜጎች ፓስፖርት የመስጠት ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡

ከመስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የቀጥታ (online Visa) አገልግሎት ይጀመራል ነው የተባለው ።

የፓስፖርት ቀጠሮ ያለፈበት ሰው ዘወትር ቅዳሜ ቀን እየመጣ መስተናገድ ይችላልም ብለዋል ዋና ዳይሬክተሯ።

ከሙስናና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘም በርካታ ደላሎች ፣ እና ህገ ወጥ አሰራር ላይ የተሳተፉ አካላት በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑንም አስረድተዋል።

በመሳፍንት እያዩ እና ሳሙኤል ወርቃየሁ

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.