ቻይና ህዝቦቼን በጨረቃ ላይ ለማሳረፍ እየተዘጋጀሁ ነው አለች
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ህዝቦቿን በጨረቃ ላይ ለማሳረፍ እየተዘጋጀች መሆኗን የሀገሪቱ ስፔስ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
ኤጀንሲው እንዳለው፥ በፈረንጆቹ 2030 የመጀመሪያውን ቻይናዊ በጨረቃ ላይ ለማሳረፍ ዕቅድ ተይዟል፡፡
ለዚህ ፕሮጀክትም የመጀመሪያው እርምጃ የሚሆነው የሰው አልባ የጨረቃ ኦርቢተር እና ላንደርን (በፕላኔቷ ወይም ጨረቃ ላይ እንዲያርፍ የተነደፈ የጠፈር መንኮራኩር) ማስወንጨፍ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ከዚያም የሚደረጉ አሰሳዎችና ሁኔታዎች ታይተው ቻይናዊው ጠፈርተኛ ከመንኮራኩሩ ዘልቀው ጨረቃ ላይ እንደሚያርፉ ሲጂቲኤን አስነብቧል።
የፕሮጀክቱ የምርምርና የግንባታ ስራ አስቀድሞ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፥ በደቡብ ቻይና ሃይናን ግዛት የሚገኘው የዌንቻንግ ሳተላይት ለፕሮጀክቱ መሳካት ግንባታ እያከናወነ መሆኑም ነው የተገለጸው።
አዲሱ የጠፈር መንኮራኩር እንደገና ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ሲሆን፥ ሦስት ሰዎችን ወደ ጨረቃ፤ ሠባት ሰዎችን ደግሞ ወደስፔስ ጣቢያ ማጓጓዝ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡
ኤጀንሲው ቻይናውያን ለአዲሱ ትውልድ ሰው ሰራሽ መንኮራኩርና ሰው ሠራሽ ጨረቃ ላንደር (በጨረቃ ላይ እንዲያርፍ ለተነደፈ የጠፈር መንኮራኩር) ስም እንዲያወጡም ጠይቋል።
#China #Space #mannedmoon
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!