Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ጣሊያን በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በትብብር እንደሚሠሩ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ጣሊያን በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ እንዲሁም በዲጂታላይዜሽን መስኮች ለጋራ ተጠቃሚነት በትብብር እንደሚሰሩ ተገለጸ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አግስቲኖ ፓለስ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ የዘርፉን ጥራት ለማሻሻል ከጣሊያንና ጋር በትብብርና በቁርጠኝነት ለሁለትዮሽ ተጠቃሚነት የሚሰሩበትን ሁኔታና የኢንቨስትመንት አማራጮችን አንስተዋል፡፡

አይ.ሲ.ቲ ለዘላቂ ልማት አጋዥ መሆኑን በማንሳት ማሕበራዊ ተጽኖውን ከፍ ለማድረግ የጋራ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተወያይተዋል።

ዘርፉን ብክነትን ለመከላከልና የተንዛዛ ቢሮክራሲያዊ አሰራርን ለማስቀረት መጠቀምም እንደሚያስፈልግም አንስተዋል፡፡

የአይ.ሲ.ቲ. ዲጂታላይዜሽን ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ እና “ክላውድ ማይግሬሽን” ላይ የእውቀት ሽግግርን ለማድረግ በመተባበር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በትብብር እንሰራለን ብለዋል።

የትብብር መሥኮቹም የአይ. ሲ. ቲ. የፓርክን እና የሰው ኃይል ልማትን እንደሚያካትቱ ተጠቁሟል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.