Fana: At a Speed of Life!

አንድ ሚሊዮን ህሙማንን የፈወሰው የካንሰር ህክምና ማዕከል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ጎልደን ኢራ” የተባለው የእንግሊዝ የበጎ አድራጎት የካንሰር ህክምና ማዕከል ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ከህመሙ መፈወስ ችሏል፡፡

የሀገሪቱ የካንሰር ጥናትና ትንተና ተቋም እንዳስታወቀው÷ ማዕከሉ ባለፉት 40 ዓመታት ውስጥ ካንሰርን ለመከላከል ባደረገው ጥረት 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ህሙማንን መታደግ ችሏል፡፡

የማዕከሉ በህክምና አሰጣጥ ሂደት ውስንነት አለበት የተባለ ሲሆን በተለይም ለሴት ታማሚዎች በቂ ህክምና እንዳልሰጠ ተገልጿል።

የበጎ አድራጎት ህክምና ማዕከሉ ስራ ዋና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ሚሸል÷ ባለፉት 40 ዓመታት ካንሰርን ለመከላከል በተደረገው ጥረት በእንግሊዝ በበሽታው የሚሞቱ ዜጎችን ቁጥር መቀነስ ተችሏል ብሏል፡፡

ዩናይትድ ኪንግደም ካንሰርን ድል እያደረገች ነው ያሉት ሚስተር ሚሸል÷ በሀገሪቱ ካለው የካንሰር ታማሚ ብዛት አንፃር አሁንም ስጋቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ካንሰር መታከም የሚችል ህመም በመሆኑ መንግስታዊ ድጋፍ እና ቁርጠኝነት ካለ ብዙ ሰዎችን ከህመሙ ማዳን እንደሚቻል አብራርተዋል፡፡

የዓለም ዓቀፉ ካንሰር ቁጥራዊ መረጃ እንደሚያመላክተው በዓለማችን በዓመት ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ህይወታቸው ያልፋል፡፡

አሜሪካ እና ካናዳ ደግሞ ከፍተኛ የካንሰር ታማሚ ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ዘጋርዲያን አስነብቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.