Fana: At a Speed of Life!

የሲንጋፖር የወደብ ባለስልጣን በኢትዮጵያ ሎጀስቲክስ ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማራ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲንጋፖር የወደብ ባለስልጣን በኢትዮጵያ በሎጀስቲክስ ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማራ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ በሲንጋፖር ከወደቡ ባለስልጣን ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በተጨማሪም በወደብ ባለስልጣኑ ጉብኝት የተደረገ ሲሆን÷ በርካታ ለኢትዮጵያ ልምድ የሚሆኑ አሰራሮች የተቃኙበት ነው ተብሏል።

ባለስልጣኑ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት የሚሰማራበትን ብሎም ልምድ የሚያካፍልበት መንገድ እንዲኖር ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ ለባለስልጣኑ ኃላፊዎች ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በበኩላቸው÷ ፈጣን ፤ ቀልጣፋና ውጤታማ የሎጀስቲክስ አገልግሎት መኖር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍና ለኢንዱስትሪ ልማት ግብዓት የሚሆኑ ጥሬ እቃዎች አቅርቦትና ኤክስፖርት ላይ የሚኖረው ፋይዳ ጉልህ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሲንጋፖር የወደብ ባለስልጣን ከ50 ዓመታት በላይ ልምድ ያለውና ከ200 ሺህ በላይ ግዙፍ ኮንቴነሮችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል ወደብን የሚያስተዳድር መሆኑን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወደቡ በኮንቴነር ማስተናገድ አቅሙ ከአለም ቁጥር አንድ ሲሆን÷ ቀልጣፋ የሎጀስቲክስ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ነው የተባለው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.