ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ከፈረንሳይ የልማት ድርጅት ተወካዮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተማና መሰረት ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ የተመራ ልዑካን ቡድን ከፈረንሳይ የልማት ድርጅት ተወካዮች ጋር ተወያይቷል፡፡
በውይይታቸውም÷ ለኢትዮጵያ ጠቃሚ የሆኑ ተጨማሪ የትብብር ፕሮጀክቶችን በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
በተጨማሪም÷ እስካሁን በድርጅቱ የተከናወኑ የትብብር ሥራዎችም የሚበረታቱ መሆናቸው በውይይቱ መነሳቱን በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡