Fana: At a Speed of Life!

የክልሉን ሕዝብ የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በትኩረት ይሠራል – አቶ እንዳሻው ጣሰው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በትኩረት ይሰራል ሲሉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ።

የሕዝቡን ፣ የአመራሩን እንዲሁም የአካባቢውን እምቅ አቅም እና ፀጋ በመጠቀም ጠንካራ ኢኮኖሚን ለመገንባት እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

የክልሉን ሕዝብ ዘላቂ ሠላም ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የክልሉ ሕዝብም ለሠላምና ልማት ግንባታው መፋጠን ከመንግሥት ጎን እንዲቆም ጥሪ ማቅረባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል ።

የገቢ መሰብሰብ አቅምን ከፍ በማድረግና የገጠር ልማትና ግብርና ተግባራትን በማጠናከር የኢኮኖሚ ልማቱን ለማፋጠን በትኩረት እንደሚሠራ ም አቶ እንዳሻው ጠቁመዋል ።

የሥራ እድል ፈጠራን በማጠናከር የንግዱ ዘርፍ ጤናማ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ በትብብር እንደሚሰራም አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.