Fana: At a Speed of Life!

አቶ እንዳሻው ጣሰው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

አቶ እንዳሻው ጣሰው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ እንዳሻው ጣሰው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ ጉባኤ በዛሬ ውሎው የክልሉን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና አፈ ጉባኤ ሹመትን አጽድቋል፡፡

በዚህ መሰረትም አቶ እንዳሻው ጣሰው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሹመዋል።

አቶ እንዳሻው የክልሉ ምክር ቤት አባል ባለመሆናቸው ነው ክልሉን በምክትል ርዕሰ-መስተዳድርነት እንዲመሩ የተመረጡት፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ከቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ ጋር የሕገ-መንግስት ርክክብ ማድረጋቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ እንዳሻው ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና በብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት ሲያገለግሉ መቆየታቸው የሚታወስ ነው፡፡

በተመሳሳይ ምክር ቤቱ ፋጤ ስርሞሎን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዋና አፈ ጉባኤ እና መነቴ ሙንዲኖን ደግሞ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሾሟል፡፡

በሌላ በኩል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የካቢኔ አባላትን ሹመት አጽድቋል፡፡

በዚህም መሠረት፦
1. አቶ ኡስማን ሱሩር – በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና የገጠር ክላስተር አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ
2. አቶ ስንታየሁ ወ/ሚካኤል – በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ
3. መሃመድ ኑርዬ (ዶ/ር) – በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ
4. አቶ ይሁን አሰፋ – የመንግስት ረዳት ተጠሪና የፖለቲካ ርዕዮተ አለም ዘርፍ ኃላፊ
5. አቶ ይግለጡ አብዛ – የክልሉ መንግስት ረዳት ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ተሾመዋል፡፡

በተጨማሪም አቶ ኤርሴኖ ሀቡሬ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እና ትክክል ጣሰው ደግሞ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.