Fana: At a Speed of Life!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥረታ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ነባሩ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልልን በአዲስ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሚል ለማደራጀት የተጠራ 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

ጉባኤው በሁለት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት አስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ ረቂቅ አዋጅና የህገመንግስት ማሻሻያ ረቂቅ ሰነዶች ቀርበው በምክርቤት አባላት ውይይት ተደርጎ ይጸድቃል።

የተለያዩ ሹመቶች መስጠትና ነባሩን ክልል በአዲስ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሚል ምስረታ መርሐ-ግብ ርም እንደሚከናወን መገለጹን ከደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.