Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ቦረና ዞን በ464 ሚሊየን ብር 34 ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች እየተገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ቦረና ዞን በ464 ሚሊየን ብር 34 “የቡኡረ ቦሩ” ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች እየተገነቡ እንደሆነ የዞኑ ትምህርት ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡

በጽህፈት ቤቱ የትምህርት ማሻሻያ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ታደሰ ቡልቶ እንደገለጹት÷ በ464 ሚሊየን ብር 134 የመማሪያ ክፍሎችን ያካተቱ 34 ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች እየተገነቡ ነው።

በትምህርት ተቋማቱ የግንባታ ስራ ላይ 40 ሺህ 800 ህዝብ እየተሳተፈ መሆኑንም አክለዋል፡፡

ትምህርት ቤቶቹ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ሲበቁ በአዲሱ የትምህርት ዘመን ከ6 ሺህ በላይ ህጻናትን የመቀበል አቅም አላቸውም ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም÷ በህዝብ ተሳትፎ አዳዲስ ተጨማሪ 16 ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን ለመስራት በእቅድ መያዙን ጠቁመዋል፡፡

ህብረተሰቡ በጥሬ ገንዘብ 234 ሚሊየን ብር እንዲሁም 230 ሚሊየን ብር የሚገመት የአይነትና የጉልበት ተሳትፎ ማድረጉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

መምህራንም ትምህርት ቤቶቹ በህዝብ ድጋፍና ትብብር እንዲሰሩ በመቀስቀስና በማስተባበር ከፍተኛ ድርሻ እየተወጡ እንደሆነም ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.