Fana: At a Speed of Life!

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በአዳዲስ ፕሮግራሞች ተማሪዎችን እንዳይቀበሉ አቅጣጫ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር በመጪው የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በአዳዲስ ፕሮግራሞች ተማሪዎችን እንዳይቀበሉ አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡

በቦርድ በጸደቁና በትምህርት ሚኒስቴር በተመዘገቡ አዳዲስ ፕሮግራሞችም ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪ መቀበል እንዳይጀምሩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) ለሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ዛሬ በጻፉት ደብዳቤ÷ በመጪው የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በአዳዲስ ፕሮግራሞች ተማሪዎችን እንዳይቀበሉ አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም÷ በቦርድ በጸደቁና በትምህርት ሚኒስቴር በተመዘገቡ አዳዲስ ፕሮግራሞችም ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪ መቀበል እንዳይጀምሩ አሳስበዋል።

የትምህርት ፕሮግራሞች ተገምግመው ከዩኒቨርሲቲዎች ተልዕኮና ትኩረት ጋር መጣጣማቸው እስኪረጋገጥ ድረስ የታቀዱ አዳዲስ ፕሮግራሞችን ለመክፈት የሚደረጉ ጥናቶችም ባሉበት እንዲቆዩ መወሰኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በ2016 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የፕሮግራሞች አከፋፈት የዩኒቨርሲቲዎችን የትኩረትና ተልእኮ ልየታ የተከተለ ሊሆን እንደሚገባም በደብዳቤው ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.