Fana: At a Speed of Life!

አድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም ታሪካዊ እሴቱን ጠብቆ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)አድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም የኢትዮጵያ ጀግኖችንና የአድዋ መልክዓ ምድርን በሚገልፅ መልኩ ታሪካዊ እሴቱን ጠብቆ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ፕሮጀክትን የግንባታ ሒደት ጎብኝተዋል።

የአድዋ ድልን ታሪካዊ ዳራ መነሻ አድርጐ እየተገነባ የሚገኘው ሙዚየሙ በመዲናዋ እስከዛሬ ከተገነቡ እና በመገንባት ላይ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች ግዙፉ መሆኑንም ነው ከንቲባዋ የገለጹት፡፡

ፕሮጀክቱ11 ብሎኮችን የያዘ፣በውስጡ የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮችን፣ የአድዋ ፈረሰኞች ማስታወሻ፣ ለሴት ጀግኖች ክብር የተሰየመ ማስታወሻ፣ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነፃነት ማስታወሻ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጀግኖችን ጉዞ የሚያሳይ ሙዚየም ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ከ300 እስከ 4000 ሰው ድረስ የሚይዙ የተለያዩ አዳራሾች የሚገኙበት ሲሆን÷ ግንባታው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ብለዋል፡፡

ፕሮጀክት ብቻ ሳይሆን ታሪክም እየገነባን ነው ያሉት ከንቲባዋ መጪውን የአድዋ በዓል የጥቁር ህዝቦች የድል የታሪክ ከፍታን በሚመጥን መልኩ በዚሁ ስፍራ ላይ በጋራ እናከብራለን ሲሉም ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልጸዋል ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.