Fana: At a Speed of Life!

የጥራት ችግር የታየባቸው ከ42 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ መድሀኒቶችና የመድሀኒት ግብዓቶች ወደ ሀገር እንዳይገቡ መደረጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2015 (ኤፍቢሲ) በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት የጥራት ችግር የታየባቸው ከ42 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ መድሀኒቶችና የመድሀኒት ግብአቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ማድረጉን የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አበራ ደነቀ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳሉት÷ መድሀኒቶች እና የመድሀኒት ግብአቶች አስፈላጊውን የጥራት መስፈርት ባለማሟላታቸው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታግደዋል፡፡

በተጨማሪም ከ33 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸውና በጉዞ ወቅት የተበላሹ እና የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው የህክምና መሳሪያዎች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ተደርጓል፡፡

ከ13 ሺህ ቶን በላይ የሚመዝኑና ከ4 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የምግብ ምርቶችም በጉዞ ወቅት በመበላሸታቸው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ተደርጓል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.