Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የቀረበለትን የአስቸኳይ ጊዜ ረቂቅ አዋጅ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአዋጅ ቁጥር 1299/2015 በ12 ድምጸ-ተአቅቦ፣ በ16 ታቃውሞ በአብላጫ ድምፅ ነው ጸደቀው፡፡

የሚንስትሮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2ዐ15 ዓ.ም ባካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባ÷ በአዋጅ ቁጥር 6/2ዐ15 የደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ ረቂቅ አዋጅ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚንስትር ተስፋዬ በልጅጌ አቅርበዋል፡፡

አቶ ተስፋዬ የአዋጁን አስፈላጊነት ሲያብራሩ÷ በአማራ ክልል በትጥቅ የተደገፈ ጥቃት መፈጸሙንና የተፈጠረውን አለመረጋጋት በመደበኛው የሕግ ሥነ- ሥርዓት ለማስከበርና ለመቆጣጠር የማይቻልበት ሁኔታ መፈጠሩን አንስተዋል፡፡

ይህም የክልሉን መንግስታዊ ሥርዓት አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ ሀገርን ከጥፋት ለመታደግ እና የሕዝቦችን ሠላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ አዋጁ አስፈላጊ መሆኑን ማስገንዘባቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ማብራሪያውን ተከትሎ በቀረበው ረቂቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎችም በፍትሕ ሚንስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ተሠጥቶባቸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.