Fana: At a Speed of Life!

19ኛው የአፍሪካ የአካባቢ ሚኒስትሮች መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 19ኛው የአፍሪካ የአካባቢ ሚኒስትሮች መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል::

ጉባኤው “የአፍሪካን የአካባቢ ችግሮች ለመፍታታት ዕድሎችን መጠቀም፣ ትብብርን ማጎልበት” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ሳንዶካን ደበበ፣ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች የአካባቢ ጥበቃ የስራ ኃላፊዎችና ተወካዮች እንዲሁም የዘርፉ የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

እስከ ነሐሴ 12 ቀን 2015 ዓ.ም በሚቆየው ጉባኤ የአየር ንብረት ለውጥ በሰዎች ላይ እያደረሰ ያለው ተፅዕኖን በሚመለከት በሚቀርቡ ሪፖርቶች፣ እያጋጠሙ በሚገኙ ችግሮችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ምክክር ይደረጋልመባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.