Fana: At a Speed of Life!

በባዮና ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ችግር ፈቺ የሆኑ 48 የምርምር ስራዎች እየተካሄዱ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽን ምርምርና ስርጸት አቅምን ለማጎልበት እና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቀው፥ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ችግር ፈቺ የሆኑ የምርምር ስራዎችን ለማከናወን በቅንጅት እየተሰራ ነው፡፡

አሁን ላይም በባዮ እና ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተመረጡ ችግር ፈቺ 48 የምርምር ስራዎች እየተካሄዱ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ከዚህ ባለፈም በስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ 62 የቴክኖሎጂ ልማቶች ምርምር ስራ በመካሄድ ላይ ይገኛል ብሏል፡፡

የኮቪድ-19 እና ኤች አይ ቪ መድሃኒት ምርምር ቅድመ ክሊኒካል ሙከራ ተጠናቆ ወደ ክሊኒካል ቴስት ለማስገባት በዝግጅት ላይ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

የኒውክሌር ሪሰርች ሬክተር ለማቋቋም መጠኑን የሚወስን ሬዲዮ አይሶቶፕ ጥናት መጠናቀቁንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የዘርፉ የምርምር ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑም የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋትና ማሳደግ ላይ በቅንጅት እንደሚሰራ ተጠቅሷል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመትም 270 የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መሰረት ልማቶች ግንባታ መከናወኑ ነው የተገለጸው፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.