Fana: At a Speed of Life!

በትራፊክ አደጋ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ሚሌ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው ከሚሌ ከተማ 14 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ሰመራ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከከባድ መኪና ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡

በአደጋው የአንድ ቤተሰሰብ አባል የሆኑ አባት፣ እናትና የ4 ዓመት ህጻን ልጅን ጨምሮ የ6 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ÷ 7 ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱ ተጠቁሟል፡፡

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች አቅራቢያ በሚገኙ የጤና ተቋማት የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የአውሲ-ረሱ ዞን ትራፊክ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የከባድ መኪና አሸከርካሪው በሕግ ቁጥጥር ስር ውሎ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገበት ነው ተብሏል፡፡

የመለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋልም ክትትል እየተደረገ መሆኑን የአፋር ክልል መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.